የአለታ ወንዶ ከተማ በሲዳማ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ከ36 ወረዳዎች እና  ከ6 የሪፎርም ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ከተማዋ በ1909 ዓ.ም የተቆረቆረች ሲሆን በአሁኑ ጊዜ  ሶስት ቀበለያት ያላት ሲሆን ለወደፊት ቀበሌያቶች ወደ ክፍለ ከተማ እንድሆኑ ጥናት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከተማዋ ከአዲስ አበባ 335 ኪ.ሜ እና ከሃዋሳ 64 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን በ6°  31' 10"  ሰሜን ላቲቲዩድ እና 38°  25' 21"  ምስራቅ ሎንግትዩድ ትገኛለች፡፡ 

የአለታ ወንዶ ከተማ  2014.16  ሄክታር የቆዳ ስፋት አላት ከተማችን ከአዲስ አበባ ቦረና ነገሌ የሚያቋርጥ መንገድ እንድሁም ከከተማዋ በንሳ፤ቦና፤አርቤጎና፤ ሀገረሰላም፤ ጩኮ፤ተፈሪኬላ፤ይርጋአለም፤ሀዋሳ የሚያገናኝ መንገድ አሏት፡፡

ከተማዋ በዙርያዋ ከሚገኙ ከተለያዩ አጎራባች ወረዳዎች ብዙ ሕዝብ የሚገበያይበት 2/ሁለት/ ቀን ቅዳሜና ረቡዕ መደበኛ ገበያ ታስተናግዳለች፡፡ ከተማዋ ከተከፈለችዉ ቀበለያት ዴላ፤መሳለሚያና ጨፈ ቀበሌዎች በሚል ስያሜ ትከፈላለች፡፡ እንድሁም ከጎሮቤት ቀበሌያቶች የሚያዋስኑዋት በሰሜን ሸእቻ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤በደቡብ ወቶ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤በምዕራብ በሌስቶን ቲቲራ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፤በምስራቅ በኩል ቡልቱማ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ያዋስኗታል፡፡